ሞዛምቢክ የፍጹም ቅጣት ምት ለምን ለተቃራኒ ቡድን ተሰጠ በሚል ጨዋታ አቋርጣ ወጣች፡፡

የፊታችን ቅዳሜ በቻን ውድድር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን የምታደርገው ሞዛምቢክ ከጋና ጋር እያደረገች የነበረችውን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አቋርጣ ወጥታለች።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በጁላይ 5 1962 ኦሎምፒክ ስታዲየም የተጀመረው ጨዋታ በ39ኛው ደቂቃ በአማዱ አማካኝነት በተቆጠረ ግብ ሞዛምቢክ ግብ አስቆጥራ መሪ በመሆን ፍልሚያው ቢቀጥልም ከ72ኛው ደቂቃ በላይ ግን አልተጓዘም።

በተጠቀሰው ደቂቃ የዕለቱ ዳኛ የሞዛምቢክ ተከላካይ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ኳስ በእጅ ተነክቷል በሚል የፍፁም ቅጣት ምት ለጋና ቢሰጡም የሞዛምቢክ ተጫዋቾች እና የአሠልጣኝ ቡድን አባላት ተቃውሟቸውን አስምተዋል።

ተቃውሞው አይሎም የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ቼኪኒዮ ኮንዴ ተጫዋቾቻቸው ሜዳውን ለቀው እንዲወጡ በማዘዝ ጨዋታው ተቋርጧል።

ዳኞች እና በስፍራው የነበሩ የጋና ብሔራዊ ፌዴሬሽን አመራሮች ሞዛምቢኮችን አስማምተው ጨዋታውን እንዲቀጥሉ ለማግባባት ቢጥሩም ሞዛምቢኮች ሀሳባቸው ሳይቀይሩ በውሳኔቸው ፀንተው ቀርተው ጨዋታው በአወዛጋቢ ሁኔታ መቋረጡን ሶከር ኢትዮጵያ ጽፏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 03 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.