በደቡብ አፍሪካ እና በኬንያ በተደረሰዉ ሥምምነት መሠረት በትናንትናው ዕለት በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት አመራሮች መካከል የመጀመሪያ ዙር የከባድ መሣሪያ ርክክብ ተደርጓል፡፡

ርክክቡ ከመቀሌ ከተማ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው “አጉላ ካምፕ” የተከናወነ ሲሆን በርክክቡ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ ታዛቢዎችም ተገኝተዋል።

በቀጠናው የተሠማራው የኢፌዴሪ ሠራዊት አመራር ሌተናል ኮሎኔል አለሜ ታደለ ÷ በመንግስትና በህዋሓት አመራሮች መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የተለያዩ ዓይነት ከባድ መሣሪያዎችን መረከባቸውን ገልፀዋል፡፡

ህወሓት ለመከላከያ ሠራዊታችን ያስረከባቸው የመሳሪያ ዓይነቶችም ብረት ለበስ ታንኮች ፣ የተለያዩ ሚሊ ሜትር መድፎች፣ ሮኬቶች፣ ዙዎች፣ ሞርተሮች እና ፐምፐን ያጠቃለለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 03 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.