“ድንቅ ነሽ” ሽልማት!

10 የሽልማት ዘርፎችን የያዘ በአይነቱ ለየት ያለ የሽልማት ስነስርዓት በቅርቡ ይካሄዳል ተባለ፡፡

በፈረጆቹ ማርች 8 ድንቅ ነሽ በሚል የአመቱ ምርጥ የሆኑ ሴቶች በ10 የሽልማት ዘርፍ እውቅና እንደሚሰጣቸው የአርኪ ፕሮሞሽን እና ኢቨንት ስራ አስኪያጅ አቶ ሸምሱ ከሪም ተናግረዋል፡፡

በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ ጠንካራ እና ብርቱ የሆኑ ሴቶች በዳኞች ተለይተው የምስጋና ሽልማት ተሸላሚ ይሆናሉ ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡ድንቅነሽ ሽልማት በበጎአድራጎት፤በህክምና፤በመምህርነት፤በጋዜጠኝነት፤በኪነጥበብ፤በውትድርና፤በፈጠራ ስራ፤በአንባሳደር፤በአመራር እና በስፖርታዊ ሙያዎች ላይ ያሉ ሴቶች ተሸላሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

በየአመቱ ለማድረግ የታቀደው ይህ የሽልምት ስነስርዓት ከመዲናችን አዲስ አበባ አልፎ ፤የክልል ከተማ ሴቶችን እንደሚያሳትፍ የአርኪ ፕሮሞሽን እና ኢቨንት ፕሮዳክሽን ክፍል ሃላፊ ወ/ሮ ስህነ-ማሪያም አበበ ተናግረዋል፡፡

ከሽልማቱ ስነስርዓት በፊት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮን ጨምሮ ከሚመለከታቸው የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ጋር በመሆን ለሽልማቱ የሚቀርቡ ሴት እጩዎችን ከአዲስ አበባ እና ከክልል ከተሞች በመለየት ተሸላሚዎች በመጨረሻው ቀን በዳኞች የሚለዩ እንደሚሆንም ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

ሽልማቱ ከማህበረሰቡ ሆነ ከተቋማት ከሚደርሱ ጥቆማዎች ባለፈ፤ ሰፊ ጥናት ተደርጎበት ትክክለኛውን ተሸላሚ የመለየት ስራ እንደሚሰራም አንስተዋል፡፡
“ድንቅ ነሽ” ሽልማት ከሚመለከተው አካል እውቅና አግኘቶ የመጀመሪያውን የሽልማት ስነስርዓት በፈረንጆቹ ማርች 8 ወይም በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር የካቲት 1/2015 እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ጥር 04 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *