በድሬዳዋ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ሪፈረንደም እንዲካሄድ አማራጭ ሐሳብ መቅረቡ ተሰምቷል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ራሱን የቻለ ክልላዊ መንግሥት እንዲሆን ወይም ከሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ወደ አንዱ እንዲጠቃለል ሪፈረንደም እንዲካሄድ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ መቅረቡ ተሰምቷል፡፡

ጥያቄው የድሬዳዋ አስተዳደር እያጋጠመው ካለው የበጀት እጥረት፣ ፍትሐዊ ያልሆነ የሀብት ክፍፍልና በዕድገት የመቀጨጭ ችግሮችን ለመቅረፍ የማይቻል ከሆነ፣ መፍትሔ ያስፈልጋል በሚል ለሁለቱ ምክር ቤቶች ቀርቧል፡፡
‹‹ድሬዳዋ በቻርተር በቀጥታ በፌዴራል መንግሥት ሥር መግባቷ በእጅጉ ጎድቷታል ነዉ የተባለው፡፡

ሌሎች ክልሎች ያመነጩትን ገቢ በቀመር ከፌዴራል መንግሥት ጋር ሲካፈሉ፣ ከድሬዳዋ የሚመነጨው ግብር ግን በቀጥታ ለፌዴራል መንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ድሬዳዋ ከምታመነጨው ትልቅ ገቢ በፍትሐዊነት ተካፋይና ተጠቃሚ እንድትሆን የግድ የክልል ጥያቄ ጉዳይ መፍትሔ እንዲበጅለት እየተጠየቀ ነው›› ሲሉ የድሬዳዋው ተወካይ አቶ አብዱልጀዋድ መሐመድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ድሬዳዋን በመወከል ሁለት የፓርላማ አባላት ያሉ ሲሆን አቶ አብዱል-ጀዋድ አንዱ ናቸው፡፡
ድሬዳዋ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ በቻርተር በቀጥታ በፌዴራል መንግሥት ሥር የምትተዳደር ሲሆን፣ ይህም ከሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የሚቀርበውን የይገባኛል ጥያቄ ለማለዘብ፣ የተወሰደ የአስተዳደር አማራጭ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *