ቱኒዚያ ህዝባዊ አመጽን ዛሬም አልተሸገረችውም፡፡

በሃገሪቱ ህዝባዊ አመጽ መቀስቀሱ ተሰምቷል፡፡
የአረብ አብዮት 12ኛ ዓመትን ለመዘከር በርካታ ቱኒዚያዊያን ወደ አደባባይ ወጥተው ነበር፡፡
ተሰባሳቢዎቹ ግን እለቱን ዘክረው ብቻ ወደ ቤታቸው አልተመለሱም፡፡

የወቅቱ ፕሬዝዳንት ካሲ ሳይድ ላይ የኢኮኖሚ ቀውስ፣የስራ አጥነት ችግርን እና የኑሮ ውድነትን በማንሳት የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡
በዚህም ፖሊስ ከተሰብሳቢዎች ጋር ሲጋጭ የሚያሳዩ ምስሎች ተለቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ካሲ ሳይድ ባለፈው ወር የሃገሪቱ ዜጎች 11 በመቶ ብቻ ድምጽ በሰጡበት ምርጫ ነበር ወደ ሃላፊነት የመጡት፡፡
አር ቲ ኒውስ እንደዘገበው ገና ከጅሩ በፕሬዝዳንቱ ላይ የሰላ ትችት እየተሰነዘረባቸው ይገኛል፡፡

መሳይ ገ/መድህን
ጥር 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *