ከበዓል ጋር ተያይዞ የኤሌክትሪክ አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ይደረግ—የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ የዕምነቱ ተከታዮች ስፍራዎችን ሲያስውቡ የኤሌክትሪክ አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳሰበ።

በየዓመቱ ጥንቃቄ በጎደለው የማስዋብ ሥራ ወቅት ከኤሌክትሪክ ንክኪ ጋር በሚፈጠሩ አደጋዎች በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እንደሚደርስ አገልግሎቱ አስታውሷል።

የማስዋብ ሥራዎች ለኤሌክትሪክ አደጋ ሊያጋልጡ ስለሚችሉ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊከናወኑ እንደሚባ አገልግሎቱ አሳስቧል።

ድንገተኛ የኤሌክትሪክ አደጋ ካጋጠመ በ905 ነፃ የጥሪ ማዕከል በመደወል ማሳወቅ እንደሚቻልም አገልግሎቱ ጠቅሟል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.