በመዲናዋ የጥምቀት በዓል ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር የተከለከለ ነው ሲል የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ አዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጥር 08 ቀን 2015 ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሐሙስ ጥር 11 ቀን 2015 አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ፤ ሞተር ብስክሌትን ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር ሥራ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ በአዲስ አበባ ከተማ በኹሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባለኹለት እግር ሞተር ብስክሌቶችን በሙሉ የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል።
የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንኑ ክልከላ መሠረት በማድረግ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግሥት እንዲጠብቁም የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የጠየቀ ሲሆን፤ ክልከላውን በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 08 ቀን 2015 ዓ.ም











