የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ በአደጋ ምክንያት ተዘጋ።

የፈጣን መንገድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ኢንስፔክተር ብርሃኑ ኃይለሚካኤል ለኢትዮ ኤፍኤም እንዳስታወቁት የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ በአደጋ ምክንያት ተዘግቷል ብለዋል፡፡

ትላንት ምሽት 4:45 በአዳማ ክፍያ ጣቢያ በአጋጠመ የእሳት አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 10 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት መዉደሙ ይታወሳል ::

ይህን ተከትሎ ለጊዜው የፍጥት መንገዱ አገልግሎት መስተጓጎሉን ሰምተናል፡፡

በዚህም ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ አደማ የሚያቀኑ አሽከርካሪዎች ሃምሳ ስድስት ወይንም በአሮጌው የአዳማ መንገድ መጓዝ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ሁለተኛዉ አማራጭ በስልሳ ወይንም (ምእራብ አዳማ ) በኩል አማራጭ መንገድ አድርገው መጠቀም እንደሚችሉ የአካባቢዉ የትራፊክ ፖሊሶች ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቀዋል፡፡

ይህንን የሚያስተባብሩ ጠቋሚ የደህንነት ሰራተኞች እንደሚገኙ በስራፍው የሚገኙት የፈጣን መንገድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ኢንስፔክተር ብርሃኑ ኃይለሚካኤል ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

መንገዱ በፍጥነት ተስተካክሎ ለተሸከርካሪ ክፍት እንደሚሆንም ኢትዮ ኤፍኤም ሰምቷል፡፡

ትናንት ምሽት ለደረሰው የእሳት አደጋ ምክንያት የሆነዉ የአበሻ አረቄ በርሜል የጫነ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ በእንቅስቃሴ ላይ እንዳለ በመቃጠሉ ነዉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ሌሎች ሶስት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸዉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በሰዓቱ እሳቱ ተባብሶ በተሽከርካሪዎች እና አንድ የክፍያ ጣቢያ ትኬት ቆራጭ በጥቅሉ የ4 ሰዎች ህይወት ወዲያው ሊያልፍ መቻን ነግረውናል፡፡

ተጨማሪ አራት ሰዎችም ከባድ የቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸዉ በአዳማ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ ብለውናል።

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ጥር 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *