የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኗል፡፡

በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዛሬ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታውቋል፡፡

በኢንተርፕራይዙ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዘሃራ መሃመድ ኢንተርፕራይዙ በታሪኩ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል ከባድ የትራፊክ አደጋ ባሳለፍነው ጥር 08 ቀን 2015 ዓ.ም ማስተናገዱን አስታውሰዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዝግ ተደርጎ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት 3፡30 ጀምሮም የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮ አፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.