የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 88 በመቶ መድረሱ ተነገረ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 88 በመቶ መድረሱን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበርያ ጽ/ት ቤት ነው ያስታወቀው፡፡
ጽ/ቤቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እናዳመለከተው ዜጎች ለህዳሴ ግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

በዚህም መሰረት በሀገር ውስጥ እና ከሃገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ 17 ቢሊዮን 595ሚ ሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችላል ብሏል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ከገንዘብ ባሻገር በእውቀት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸውን የተናገረው ማስተባበርያ ጽፈት ቤቱ፣ በተያዘው ወር ላይ ዓለም አቀፍ የስዕል ሲንፖዚያም እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፍ የስዕል ሲንፖዚየሙ በዓባይ ወንዝ መነሻ ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርም ነው ያስታወቀው፡፡
በዚህ ሲንፖዚየም ላይ ከ23 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የስዕል ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

ኢትዮ አፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.