ተማሪዎቹ የተቀጡት በሦስት ዓይነት የፈተና ደንብ ጥሰቶች ሲሆን፣ በግል የፈተና ደንብ ጥሰት 1 ሺሕ 151 ተማሪዎች፣ በቡድን የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 5 ሺሕ 329 ተማሪዎች፣ እንዲሁም ፈተና ጥለዉ በመሄድ የተቀጡ 13 ሺሕ 690 ተማሪዎች ናቸዉ።
በተጨማሪም በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 985 ሺሕ 354 ተማሪዎች መካከል፣ 77 ሺሕ 98 ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና አልወሰዱም።
እንዲሁም ፈተናውን ከወሰዱ 908 ሺሕ 256 ተማሪዎች መካከል፣ በፈተና ደንብ ጥሰት የተቀጡ ተማሪዎችን ሳይጨምር 896 ሺሕ 520 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም











