የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ4 ሺህ 401 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ለታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረገው በይቅርታ ቦርዱ ተመርምሮ መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው የክልሉ ምክር ቤት ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በክልሉ ፍትሕ ቢሮ አቅራቢነት በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ በወሰነው መሰረት እንደሆነ ታውቋል፡፡

የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑት በይቅርታ አሰጣጥ መመሪያው ላይ የተገለፁ፣ የእስራት፣ የዕድሜና የጤና መስፈርቶችን ያሟሉ ናቸው መባሉን ከክልሉ ፍትሕ ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ሆኖ በሙስና ወንጀል ተከሰው 10 ዓመት እና ከዛ በላይ የተፈረደባቸው፣ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ላይ የሚፈፀም አስገድዶ መድፈርና ጠለፋ ወንጀል የፈፀሙ ይቅርታው አያካትታቸውም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተፈረደባቸው፣ የሀሰት ገንዘብ መስራት ወይም ማዘዋወር ወንጀል የተቀጡ ይቅርታው እንደማያካትታቸው ተጠቅሷል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ያሳዩትን መልካም ስነ-ምግባር ለበደሉት ህብረተሰብ በልማት ሊክሱት እንደሚገባ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.