ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የህዝበ ውሳኔ ድምፅ እየሰጡ ሲሆን በአንድ የምርጫ ጣቢያ ሂደቱ ተቋርጧል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው በወላይታ ዞን ስር በሌ የምርጫ ማዕከል ‘ሶርቶ’ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ ውስጥ የህግ ጥሰት መፈፀሙን አረጋግጫለሁ ብሏል።
በምርጫ ጣቢያው ድምፅ በመስጠት ሂደት ወቅት የቀበሌ አስተዳደር ሀላፊዎች በሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ በመገኘት 105 የሚሆን የግለሰብ ጊዜያዊ መታወቂያዎችን ድምፅ ለመስጠት ለተሰለፋ ዜጎች በማደል ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል።
በዚህም የህግ ጥሰቱ እስከሚጣራ ድረስ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንዲያቋርጥ መወሰኑ ታውቋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም











