በከተማዋ የሞተር ብስክሌት እና የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ማሽከርከር ስለመከልከሉ!

በአዲስ አበባ ከሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር ተያይዞ፤ ከዛሬ የካቲት 1/2015 ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ሞተር ብስክሌት እና የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት ከዛሬ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 5/2015 አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ በከተማዋ የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።

እንዲሁም፤ ሞተር ብስክሌቶችን ከዛሬ የካቲት 1/2015 ጀምሮ 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ እስኪጠናቅ የካቲት 13/2015 አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑንም አስታውቋል።

ኤጀንሲው ክልከላው የሚመለከተው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር ሥራ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ በአዲስ አበባ ከተማ በኹሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባጃጆችን፣ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶችንና በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን ጭምር መሆኑን ገልጿል፡፡

የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች፣ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ይሄንኑ ክልከላ መሰረት በማድረግ፤ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው ያሳሰበ ሲሆን፤ ይህንን መልዕክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

የኢትዮጵያዊያንየካቲት 01 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.