በተርኪዬና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 16 ሺህ ማለፉ ተነገረ፡፡

በሁለቱ ሀገራት በተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ16 ሺህ መሻገሩ ታዉቋል፡፡

በአደጋዉ 12 ሺህ 8 መቶ 73 የተርኪዬ ዜጎች ህይዎታቸዉን ሲያጡ በሶሪያ ደግሞ 3 ሺህ 1 መቶ 62 ሞተዋል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች በአደጋዉ የተጎዱ ዜጎችን ለማዳን እየተረባረቡ እንደሚገኙም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም ተሰግቷል የሀገሪቱ ዜጎችም መንግስት ለነፍስ አድን ሥራዉ
የሰጠዉ ትኩረት በቂ አይደለም በሚል እየተቹ ነዉ፡፡

በተጨማሪም በአደጋዉ ከ8 ሺህ በላይ ህንጻዎች መዉዳማቸዉን የገለፀ ዘገባዉ ለዚህም የኮንስትራክሽን ጥራት መጓደል አደጋዉን አባብሶታል እየተባለ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
የካቲት 02 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.