የካቲት 1 ቀን ሌሊት 7:34 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታዉ መነን አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ በአጋጠመ የእሳት አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
በአደጋዉ አንድ እናት ከስምንት አመት ልጇ ጋር ህይወቷ ያለፈ ሲሆን የሟች የትዳር አጋርና የህጻን ልጁ አባት በቃጡሎዉ ጉዳት ደርሶባቸዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል።
በእሳት አደጋዉ አራት መኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ተስፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
አደጋዉን ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ አንድ አምቡላንስ ከ24 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን እሳቱን ለመቆጣጠር 2:25 ሰዓት እንደፈጀ ከእሳት እና ድንገተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።
በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 02 ቀን 2015 ዓ.ም











