የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ የአዲስ አበባ ቢሮ ተዘረፈ::

ኢሰመጉ በአዲስ አበባ የከፈትኩት አዲስ የምርመራ ቢሮ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ በሌሊት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተሰብሮ ተዘርፌያለሁ ብላል።
በዘረፋውም የክፍል ኃላፊው ላፕቶፕ ኮምፒውተር ተወስዷል ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ቢሮው ውስጥ ሌሎች ላፕቶፖች ሳይወሰዱ ጅምር የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራዎችን የያዘው የኃላፊው ላፕቶፕ ብቻ ተለይቶ መወሰዱ፣ የቢሮ ሰበራው “የተጠና” እና “ብርበራ የሚመስል” ድርጊት መሆኑንም ኢሰመጉ ገልጿል።

ኢሰመጉ፣ መንግሥት በተቋሙና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ላይ እየደረሱ ያሉ ጫናዎችንና ማስፈራሪያዎችን ባስቸኳይ እንዲያስቆም እና ጥበቃ እና የሕግ ከለላ እንዲሰጥም ጠይቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 07 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *