የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለሮሂንጊያ ስድተኞች የሚያደርገውን የምግብ እርዳታ ለመቀነስ ማሰቡ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በባንግላዲሽ በስደተኛ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙትን የሮሂንጊያ ስደተኞች በበጀት እጥረት ምክንያት እርዳታ ለመቀነስ ማሰቡን አስታውቋል፡፡

ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑ ቢታወቅም የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የተባበሩት መንግስታት የምግብ ኤጀንሲ ለስደተኞች የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማቋራጥ ማሰባቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

ወርሃዊ አበል ከግንቦት ወር ጀምሮ በ17 በመቶ ቀንሶ ወደ 10 ዶላር ዝቅ እንደሚል ነው የተገለጸው፡፡

እንደ ድርጅቱ ማስጠንቀቂያ ከሆነ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ካልተገኘ በስተቀር ቅነሳ ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል ብሏል፡፡

በአብዛኛው የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ማይናማር ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ወደ ባንግላዲሽ የተሰደዱ ሲሆን ቁጥራቸውም ከ750ሺህ በላይ መሆኑ ይነገራል፡፡

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.