በደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ የሚገኙት የኢግቦ ጎሳ አባላት የሆኑት የቢፋራ ሰዎች፣ ይህንን ጥቃት ሳያደርሱ እንዳልቀሩ መጠርጠሩን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡
በተከፈተዉ ጥቃትም ቢያንስ 8 የፖሊስ አዛዦች መገደላቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ይህ ግድያ 90 ሚሊየን የናይጄሪያ ዜጎች ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ቡሀሪን የሚተካ መሪ ለመምረጥ በተመዘገቡበት ማግስት መሆኑ ነገሮችን አወሳስቧቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

ጥቃቱ የፊታችን ቅዳሜ ለሚካሄደዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚወጡ ዜጎችን ደህንነት የሚጠብቁ የፖሊስ አባላት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል መባሉንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በእስከዳር ግርማ
የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም











