የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አጠቃላይ ካፒታሉ 36 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ባለፉት ሶስት አመታት ከነበሩበት ጫናዎች ወጥቶ የተሻለ ስራ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታውቆ አጠቃላይ የባንኩ ካፒታል 36 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ይህንን ያስታወቀው ለአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አንቀሳቃሾች ስልጠናን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሃንስ አያሌው እንደተናገሩት፣ ባለፉት ሶስት አመታት ከፍተኛ ውድቀት ላይ የነበረው ባንኩ አሁን በትክክለኛ መንገድ እየተጓዘ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ከሶስት አመት በፊት የባንኩ ካፒታል 7.5 ቢሊዮን እንደነበረ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ይባስ ብሎም ሁለት ቢሊዮን ብር የደረሰበት ጊዜም ነበር ብለዋል፡፡

ልማት ባንክ ከአለም ባንክ ባገኝው የገንዘብ ድጋፍ ለአራተኛ ዙር የአነስተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና አንቀሳቃሾች ስልጠና በዛሬው እለት በይፋ በማስጀመር ላይ ይገኛል፡፡

ዓለም ባንክ ለዚህ ፕሮጀክት 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዳደረገም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
ለዚህ ስልጠና ከ400 ሺህ በላይ ሰልጣኞች በመላው ሃገሪቱ የተመዘገቡ ሲሆን፣ በዛሬው እለትም 112 ሺህ ያህሉ ስልናቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል፡፡

ስልጠናውም በ56 ከተሞች እና በ95 ማዕከላት እንደሚሰጥ የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሃንስ አያሌው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.