ፑቲን ከአሜሪካ ጋር የነበራቸውን የኒውክሌር ስምምነት ማቋረጣቸውን አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በተመለከተ የነበራትን ስምምነት ማክበር አይጠበቅባትም ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በሞስኮ ባደረጉት ረጅም ንግግር፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ኪየቭ ያደረጉትን ያልተጠበቀ ጉብኝት ጨምሮ በበርካታ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ማብራራያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም ጦርነቱ የተቀሰቀሰው እና የተስፋፋው “አሜሪካ እና አጋሮቿ የኃይል ጥማት ስላለባቸው ነው” በማለት ምዕራባውያኑን ወቅሰዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይድን በዚህ ሰዓት ከኔቶ ምስራቃዊ አጋሮች ጋር ለመመካከር ፖላንድ ይገኛሉ።
የአልጀዚራ ዘገባ እንደሚያሳየው ከሆነ የሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ቢያንስ 8ሺህ ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡

አቤል ደጀኔ
የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.