እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የአየር ጥቃት መክፈቷ ተነገረ፡፡

የእስራኤል አየር ሃይል ከፍልስጤም ሮኬት መተኮሱን ተከትሎ ጋዛን መደብደብ መጀመሩ ታወቋል፡፡

በትናትናዉ ዕለት የእስራኤል ጦር አሸባሪዎችን ለማደን ነዉ በሚል በዌስት ባንክ በወሰደዉ ጥቃት 11 ዜጎች መገዳለቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

ይህንንም ተከትሎ ስዴሮትና አሽኬሎን የተሰኙት የአስራኤል ከተሞች የሮኬት ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡

ለሮኬት ጥቃቱ ከፍልስጤም በኩል እስካሁን ኃላፊነተ የወሰደ አካል እንደሌለ አልጄዚራ ዘግቧል፡፡በዛሬዉ ዕለትም እስራኤል ለሮኬቱ የመልስ ምት ጋዛ ላይ የአየር ጥቃት ከፍታለች ነዉ የተባለዉ፡፡

በአባቱ መረቀ

የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.