ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም አቀፉ ገበያ ጋር የሚያገናኝ ቴክኖሎጂ ሃይከል LLC የተባለው የቴክኖሎጂ ድርጅት ይፋ አደረገ።

አሜሪካን ሃገር የሚገኘው ሃይከል ኤል ኤል ሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃይከል ቴክኖሎጂስ ኃላ/የተ/የግ/ማ በሚል ስያሜ ቅርንጫፍ በመክፈት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ የሆነውን የሳስ እና ማስ ኢኮመርስ ስራ በመዘርጋት መላው የኢትዮጵያን ገበያ ከአለም አቀፉ ገበያ ጋር ለመቀላቀል ማቀዱ ነው የተነገረው።

ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች እና ግለሰቦች ያለ ምንም የውጭ ሃገር ንግድ ፈቃድ፣ የመርቻንት አካውንት የውጭ ባንክ አካውንት እና የዶላር አካውንት ሳያስፈልጋቸው ከአንደኛው የውጭ ሃገር ወደሌላ የውጭ ሃገራት የንግድ፣የፍሪላንስግ ስራ ካሉበት ሆነው እንዲሰሩ ለማድረግ ትልቁን ስራ በመስራት ለመላው ኢትዮጵያውያን ታላቅ እድል ማመቻቸቱ ተገልጿል።

ይህም እድል የኢትዮጵያ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በዶላር እጥረት ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ የሚያደርጋቸውን ችግር በመቅረፍ የሚፈልጉትን ስራ በቀላሉ እንዲሰሩ ፣ የኢትዮጵያ ባንኮችን ከሃይከል ቴክኖሎጂስ ጋር በማጣመር ድርጅቱ በሚሰራባቸው 253 ሃገራት በሙሉ አብረው እንዲሄዱና ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ደንበኞችንም በማገልገል ከፍተኛ የዶላር ምንዛሬ እንዲያገኙ ያስችላል መባሉን ባልደረባችን እሌኒ ግዛቸው ዘግባለች።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.