ኢትዮጵያ በአዉሮፓ ህብረት በሚደገፉ አህጉራዊ ፕሮጀክቶች በኩል 320 ሚሊዮን ዮሮ ተጠቃሚ ሆነች።

የአዉሮፓ ህብረት “የስደት ዕድሎቹና እና ተግዳሮቶቹ” በሚል በብሔራዊ ቲአትር ያዘጋጀዉ የአጭር ፊልም ዉድድር ፍፃሜዉን አግኝቷል።

የአጭር ፊልም ዉደድሩ በስደት ላይ ያተኮረ ሲሆን ድምፅ የመስጠቱ ስራ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሚሰጠዉ በተጨማሪ የአዉሮፓ ህብረት ቡድን መሪ አማባሳደር ሮናልድ ኮቢያ፣ድምፃዊ ካስማሰ እና የፋሽን ዲዛይነርና ስራ ፈጣሪ ማህሌት አፈወርቅ “ማፊ” ተሳትፈዉበታል።
ለአሸናፊዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የአዉሮፓ ህብረት ለአፍሪካ የአደጋ ግዜ ትረስት ፈንድ ከ5 ቢሊዮን ዮሮ በላይ መድቢያለዉ ያለ ሲሆን ይህም 88 ፐርሰንት በላይ መዋጮዉ ከአዉሮፓ ህብረት የሚገኝ ነዉ ተብሏል።
የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣የተመድ ኤጀንሲዎች እና አገራዊ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 246 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል ተብሏል ።

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.