12 ህፃናትን ጨምሮ 59 ስደተኞች ህይወታቸው አለፈ፡፡

ስደተኞችን የተሸከመች መርከብ በጣልያን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ መስጠሟ ተነግሯል፡፡

በ100ዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ተሸክማ ስትጓዝ የነበረቸው መርከብ ከባድ አየር ንብረት ባለበት በጣልያን ወደብ አቅራቢያ መስጠሟ ነው የተገለጸው፡፡

በጣልያኗ ደቡብ ክልል ካላብሪያ ክሮቶኔ የወደብ ከተማ ላይ በደረሰው የመርከብ መስመጥ አደጋ 12 ህፃናትን ጨምሮ 59 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

መርከቧ ከጥቂት ቀናት በፊት ከቱርክ ተነስታ ከአፍጋኒስታን፣ ኢራን እና ከበርካታ ሀገራት ስደተኞች ጋር በመጓዝ ላይ የነበረች ሲሆን በእሁድ እለት በካላብሪያ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ በምትገኘው ስቴካቶ ዲ ኩትሮ በተባለው የባህር ዳርቻ ሪዞርት አቅራቢያ በተከሰተ አውሎ ንፋስ ሰጥማለች።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንደገለፁት ከሆነ አስካሆን የሟቾች ቁጥር 59 ሲሆን ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል ፍንጭ ሰተዋል፡፡

ከተረፉት መካከል አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ምርመራ እየተደረበት እንደሚገኝ የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.