በኢትዮጵያ ያሉ መድሃኒት አምራቾች ማምረት ካለባቸው 8 በመቶውን ብቻ እያቀረቡ ነው ተባለ።

በኢትዮጵያ ካሉት 13 የሚደርሱ መድሃኒት አምራቾች ማምረት ካለባቸው 40 በመቶ የመድሃኒት አቅርቦት ውስጥ ማቅረብ የቻሉት 8 በመቶውን ብቻ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ አምራቾ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ዋቅቶላ እንዳሉት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የአመራር ክህሎት ማነስ ዘርፉን እየፈተኑት ይገኛሉ።

በተጨማሪም የጥሬ እቃዎች ዋጋ መዋዠቅ፣በበቂ መጠን ያለመገኘት፣ በተጠበቀበት ጊዜ ያለመምጣት የሚጠቀሱት ናቸው፡፡

አቶ ዳንኤል ጨምረውም መንግስት በጤናው ዘርፍ ላይ ያስቀመጠውን ፖሊሲ ማሻሻል እና በደምብ መመልከት አለበት ብለዋል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ አሁን ላይ ያለው የመንግስት ፖሊሲ ( ከውጭ ማስገባትን) የሚደግፍ በመሆኑ ክለሳ ሊደረግበት ይገባል ብለዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.