የጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ሊመሰረተ ነው፡፡

ጎጎት የተሰኝ የጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ ሊመሰረት መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ከፓርቲው አደራጅ ኮሚቴ ያገኝነው መረጃ እንዳመለከተው ጎጎት ፓርቲ የሚመሰረተው የጉራጌን ህዝብ እየደረሰበት ካለው አስተዳደራዊ በደል እና ስጋት ለመታደግ ነው፡፡

ፓርቲው ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የፓርቲ ማደራጃ ፍቃድ ወስዶ ለሃገራዊ ፓርቲ የሚያበቁ ቅድመ ሁኔታዎች በሟሟላት ላይ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በምስረታ ላይ የሚገኝው ጎጎት ፓርቲ፣ የመጀመርያ የምስረታ ጉባኤውን በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ እንደሚያደርግ ነው ከፓርቲው ያገኝነው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

“ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ” የሚል ስያሜን የያዘው አደረጃጀት የምስረታ ጉባኤውን በማካሄድ የፓርቲውን የስራ አስፈጻሚዎችንና ማዕከላዊ ኮሚቴዎችን ይመርጣል ተብሏል።

ጎጎት” የጉራጊኛ ቃል ሲሆን የጉራጌ አባቶች ህዝቡ በ18 መቶ ክፍለ ዘመን ገጥሞት ከነበረው የመበታተን አደጋ ለመውጣት ቃልኪዳን ያሰሩበት ስፍራ መሆኑንና አሁንም ከእንዲህ አይነቱ ስጋት ለመዳን በማሰብ ስያሜው መመረጡን አደራጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.