የቡና አፈላል ኤክስፖ ሊደረግ ነው፡፡

የኢትዮጵያዊያን ባህል የሆነውን የቡና አፈላል የሚያሳይ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የ12ቱም የኢትዮጵያ ክልል የቡና አፈላል ባህልን የሚያሳይ ኤክስፖ በመጪው መጋቢት 9 በስካይ ላይት ሆቴል የባህል አዳራሽ ይከናወናል።

በዚህ የቡና አፈላል ኤክስፖ ኢትዮጵያዊያን ቡና ሲጠጡ የሚታወቁበት የንግግር ባህል ችግሮቻችንን እንዴት እንደምንፈታ ለጎብኝዎች ይቀርባል ተብሏል፡፡

የዋርካ ኮፊ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዒዳ ሙስጠፋ እንደተናገሩት፣ ይህ ባህላችን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንደዚህ አይነት ኤክስፖዎች ማዘጋጀት እና ለዓለም ማህበረሰብ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በዋርካ ኮፊ አዘጋጅነት በሚከናወነው ይህ ኤክስፖ የመንግስት ሀላፊዎች፣አምባሳደሮች፣ነጋዴዎች እና በርካታ ጎብኚዎች ይካፈሉበታል ተብሏል።

ኤክስፖው ከቀኑ ስድስት ሰአት እስከ 12 ሰአት እንደሚቆይ የዋርካ ኮፊ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰዒዳ ሙስጠፋ ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.