በሃገሪቱ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የተነገረ ሲሆን፣ አሁን ላይ 23 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ባንኪንግ እየተጠቀሙ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
የብሄራዊ ባንክ የክፍያ ስርዓት ክትትልና ልማት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣የሞባይል ባምኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር 23 ሚሊዮን ደርሷል፡፡
የዜጎች የዲጂታል ክፍያ አማራጭ ፍላጎት እንዲጨምርና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ላይ ጠንካራ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባም አክለዋል።
በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከ1.7 ትሪሊዮን ብር በላይ በዲጂታል ቴክኖሎጂ መዘዋወሩንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 05 ቀን 2015 ዓ.ም











