ባንኩ ወደ ሥራ ከገባ ጀምሮ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝና በመጪው ቅዳሜ በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል።
የአማራ ባንክ አክስዮን ማህበር መርሃባ የተሰኘውን ከወለድ ነፃ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችን እንደሚከፍትም በዛሬው ዕለት በሰጠው መግላጫ ገልጿል።
ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን ተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለማሟላት በመላው ሀገሪቱ በስፋት እንደሚሰራም ታውቋል።የአማራ ባንክ አሁን ላይ 2 መቶ 30 ቅርንጫፎች በመላ ሀገሪቱ እንዳሉት አስታውቋል።
በዚህም ከ 35 ሺህ በላይ የመርሃባ ከወለድ ነፃ ደንበኞች አሉኝ ነው ያለው።
በዚህ ዓመት መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ 30 ቅርንጫፎችን እንደሚከፍትም ባንኩ ገልጿል።መርሃባ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱ የዘመኑን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
በአባቱ መረቀ
መጋቢት 07 ቀን 2015 ዓ.ም











