ለመስተንግዶ ወጪ የተፈቀደውን በጀት በብር እየተቀየረ እየተወሰደ መሆኑ ተነገረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥናት አጥንቶ በማዕከል፣በክ/ከተማ እና ወረዳ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች እና በሜሪት ደረጃ ለተሸሞ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የሚገባ ጥቀማ ጥቅም ፓኬጅ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

የመስተንግዶ ወርሃዊ ወጪ ወደ ተቋሙ ለሚመጡ እንግዶች እና ለተፈቀደላቸው አመራሮች የሻይ፣ቡና እና ለተለያዩ መስተመንግዶ ወጪ ብቻ የተፈቀደለት ቢሆንም በአንድ አንድ ክ/ከተሞች እና ወረዳዎች ይህንን የመስተንግዶ በጀት ወደ ብር በመቀየር እየወሰዱ መሆኑን ጣብያችን ለማወቅ ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች ክ/ከተሞችና ወረዳዎች ላይ በብር እየቀየሩ እየወሰዱት እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የከተማ አስተዳደሩም በዚህ ተግባር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ አመራሮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቡንና ከዚህ በኃላ በድርጊቱ ተሳትፈው የሚገኙት ላይ እርምጃ እወስዳለው ማለቱን ሰምተናል፡፡

በአቤል ደጀኔ
መጋቢት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *