በብዝሃ ሕይወት ሳይንቲስትነት አንቱታን ያተረፉት ሎሬት ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር ባደረባቸው ሕመም በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ እና ተከራካሪ የነበሩት ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር ከአባታቸው ከቄስ ገብረእግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ መዓዛ ወልደ መድኅን በትግራይ ክልል ዐድዋ ርባገረድ መንደር የካቲት 12 ቀን 1932 ዓ.ም ነበር የተወለዱት።
ሎሬት ዶ/ር ተወልደብርሃን በሕይወት ዘመናቸው ለአገራቸው ያበረከቱት አስተዋጽኦ እና አርዓያነታቸው በጉልህ ቀለም ከሚጻፍላቸው ጀግና ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ነበሩ።
በብዝሃ ሕይወት ጥናት እና ምርምርም በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችንም ማግኘት ችለዋል።
ዶ/ር ተወልደ ብርሃን የሦስት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም











