የረመዷን ፆም ዛሬ ጨረቃ ከታየች ነገ፣ ካልሆነ ግን ከነገ በስቲያ ይጀምራል ሲል የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ገለጸ።

የ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዷን ፆም ማክሰኞ (ዛሬ) ጨረቃ ከታየች ረቡዕ (ነገ)፣ ካልሆነ ግን ሐሙስ (ከነገ በስቲያ) እንደሚጀምር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

ፍርድ ቤቱ የ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዷን ፆምን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል።

“ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንኳን ለ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዷን ጾም በሰላም አደረሳችሁ፤ ለዚህ የተከበረ ታላቅ ወር ረመዷን በሰላም ላደረሰን አላህ ምስጋና እናቀርባለን” ብሏል ፍርድ ቤቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ።

ሕዝበ ሙስሊሙ የእርስ በርስ መደጋገፍ እና መረዳዳት ተግባሩን በፆሙ ወቅት ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥልበትም ፍርድ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

ለመላው ኢትዮጵያውያን እና የዓለም ሙስሊሞች ወሩ የጤና፤ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ፍርድ ቤቱ መልካም ምኞቱን ገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.