የአሜሪካን ክስ አልቀበለውም…ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀረበባትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫዉ።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ መወንጀል ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ በመግለጫ የጠቆመው።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጮችን ለመለየት ብሔራዊ ምክክር ለመጀመር በተዘጋጀችበት ወቅት ላይ የወጣ በመሆኑም መግለጫው ወቅቱን ያልጠበቀ ነው ብሎታል።

ባለፈዉ ሳምንት የአሜሪካዉ የዉች ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በአዲስ አበባ በነበራቸዉ ቆይታ ከመንግስት ከፍተኛ ባለሰልጣናት ጋር ዉጤታማ ዉይይት ማድረጋቸዉን መንግስት አስታዉቆ ነበር፡፡
ይሁን አንጅ አንቶኒ ብሊልንከን ወደ ሀገራቸዉ ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስትን መክሰሳቸዉ ታወቋል፡፡

በአባቱ መረቀ

መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.