ከአሳሳች መረጃዎች ራሳችሁን ጠብቁ—የኢትዮጵያ አየር መንገድ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳለው በተቋሙ ስም “እንቻለው ልጥገብ የአቪዬሽን ተቋም” ብሎ የሚጠራ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሰራተኞችን ለቅጥር እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍቃድ የሰጠው በማስመሰል ሰዎችን በማሳሳት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የከፈተውን የሂሳብ አካውንት በመጠቀም ገንዘብ በመቀበል ላይ እንደሚገኝ አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

ይሁንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተጠቀሰው ድርጅትም ይሁን ከየትኛውም አካል ሰራተኞችን ለቅጥር ከሚያቀርብ ድርጅት ጋር የስራ ስምምነት እንደሌለው ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአየር መንገዱ የመረጃ ትስስር ገጾች ላይ ተመልክቷል፡፡

አየር መንገዱ ሰራተኞችን የሚቀጥረው በራሱ ዌብሳይት በመግለጽ ሲሆን ከተቀጣሪዎች ምንም አይነት ክፍያ እንደማይቀበልም ነው የገለጸው፡፡

በመሆኑም ስራ ፈላጊዎች በነዚህ ድርጅቶች ሳትታለሉ ለስራ ቅጥር መረጃዎች የአየር መንገዱን ድረገጽ Ethiopian Airlines-Careers ብቻ እንድትከታተሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.