ሩሲያ አዲስ ወታደራዊ ሳተላይት ወደ ጠፈር ማስወንጨፏ ተነግሯል።
የሩስያ መከላከያ ሚኒስትር የሃገሪቱ የስፔስ ማዕከል፣ወታደራዊ ሳተላይት ወደ ኦርቢት መላኩን አስታውቀዋል፡፡
“ሶዩዝ 2.1” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ወታደራዊ ሳተላይት አርካንግልስክ ክልል ከሚገኘው ከፕሌሴስክ ወታደራዊ መንደር መወንጨፏን አር.ቲ ዘግቧል።
ሩሲያ ያስወነጨፈችው አዲሱ ወታደራዊ ሳተላይት ኦርቢት ላይ ደርሶ መሬት ላይ ካለ የመቆጣጠሪ ጣቢያ ጋር ግንኙት ማድረጉን እና በአግባቡ ስራ መጀመሩም ተነግሯል፡፡
ሳተላይቱን በሩሲያ ኤሮስፔስ ኃይል ውስጥ የጠፈር ተዋጊዎች ያስወነጨፉት ሲሆን፤ ተዋጊ ሃይሎቹ ሳተላይቱን ሶዩዝ 2.1 በተባለ ዘመናዊ ማስወንጨፊያ ተሸከርካሪ በመጠቀም የተሳካ ስራ መስራታቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም











