በጦርነቱ ምክንያት ካዝናዋን ያራቆተችው ዩክሬን ለብድርና እርዳታ እጇን መዘርጋት ከጀመረች ዋል አደር ብላለች፡፡
ጦርነቱ ሲጀመር በርቺ ያሏት ሃገራትና ተቋማት አሁን ችግር ላይ ስትወድቅ ከእርዳታ ይልቅ ብድር እንድትወስድ ግፊት እያደርጉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በዚህም አይ ኤም ኤፍ ከቀጥተኛ ድጋፍ ይልቅ በብድር መልኩ ወደ ሃገሪቱ ገንዘብ ፈሰስ ለማድረግ ካዝናውን እየፈተሸ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የብድር ሂደቱ በቀጣዮቹ አራት ዓመታት የሚፈጸም ሲሆን የመጀመሪያዎቹ 18 ወራት ከፍተኛውን የበጀት ጉድለት ለመሸፈን፤የተቀረው ደግሞ ሀገሪቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ያለመ ነው ተብሏል።
በፈረንጆቹ 2022 የዩክሬን ኢኮኖሚ ከነበረበት 30 በመቶ ገደማ ማሽቆልቆሉን የአርቲ ዘገባ ያመለክታል፡፡በተጨማሪም የባንክ ስርዓቱን ከሙስና ለማፅዳት ጥረት ቢደረግም መሻሻል እንዳላሳዬ ተገልጿል፡፡
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም











