ባለፉት 5 ዓመታት ዉስጥ እኛ የወሰድነዉ አንድ ዶላር ኮሜርሻል ብድር የለም- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

ነገር ግን ከብድሩ ላይ 1.7 ቢሊየን ዶላር ከፍለናል ነዉ ያሉት፡፡

የአገራችንን ኢኮኖሚ የሚገዳደሩ ብዙ ጉዳዮች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከዉስጥ ያለዉ እና ከአለም ገበያ የምናስገባዉ እራሱን የቻለ የዋጋ ንረት፣ ምርትና ፍላጎት ለማገናኘት ከባድ የሆነዉ የመሰረተ ልማት ክፍተት እና በፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለዉ ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ኢኮኖሚያችንን የሚገዳደር ነዉ ብለዋል፡፡

አገራችን ላይ ባለዉ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ዜጎች ተጎጂ መሆናቸዉ ግልጽ ነዉ ያሉ ሲሆን፣ ለዚህም እንደምክንያት ለ 20 ዓመታት በተከታታይ ያደገዉ የኑሮ ዉድነት እና አለመግታት መቻላችን ችግሩን አባብሶታል ብለዋል፡፡

ሌላኛዉ ደግሞ የአምራችና የሸማች ፍላጎት አለመጣጣም ሲሆን ከዚህ ዉጪ ደግሞ ጦርነት እና ድርቅ ምክንያቶች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡

በጦርነት እና ድርቁ ምክንያት ደግሞ ለአገራችን የሚሰጠዉ የብድር እና የድጋፍ ስራዉ መቀዛቀዙን ነዉ ያነሱት፡፡

ለዚህም መፍትሄ የሚሆነዉ አቅርቦት በተለይም ምርት ላይ መስራት መሆኑን ገልጸዉ መንግስት ከሚበጅተዉ በጀት ዉስጥ 59 በመቶዉን ለድህነት ቅነሳ ስለሚያዉል ይህንን በመጠቀም ሁኔታዎችን ማሻሻል ያስፈልጋል ነዉ ያሉት፡፡

በዚህ በ 2 ወይም 3 ወራት ዉስጥ የተከሰተዉ የዋጋ ንረት እንደሚባለዉ የከፋ አይደለም፣ አቅርቦቱን በመጨመር እና ሁኔታዎችን በማሻሻል የሚረጋጋ እንደሚሆን ተስፋ አለን ብለዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.