ከ825ሺ በላይ አሽከርካሪዎች በደንብ ጥሰት መቀጣታቸው ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመነት በዘጠኝ ወራት ግዜ ውስጥ ማለትም አስከ መጋቢት 20 ባለው ግዜ ውስጥ በተለያዩ እርከነ የደንብ ጥሰት ላይ የተሰማሩ ከ825ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልፀዋል፡፡

ከእርከን 1 አስከ 5 ባለው የደንብ ጥሰት ላይ የተሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የገለፁት የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ታረቀኝ በርካታ ሰራዎች እየተሰራ ቢሆንም ከቀን ወደ ቀን አደጋዎችና ደንብ ጥሰቶች መበራከታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህንንም ለማረም እርምጃ ከመውሰድ በዘለለ በትምህርት ካሪኩለም እንዲካተት የማድረግ ስራ መስራታቸውንና ከትምህርት ቤቶች ጋር በጋራ እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

አቶ አማረ አክለውም በስድስት ወራት ውስጥ ከሐምሌ 1 አስከ ታህሳስ 30 16ሺ በላይ አደጋዎች በከተማዋ ማጋጠሙን ገልፀው በቀን 1 የሞት አደጋ እንደሚያጋጥም የገለፁ ሲሆን በአጠቃላይ በአካል ጉዳት ላይ የነበሩን ጨምሮ በስድስት ወራ ውስጥ 217 ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠመ ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም በቀን ቢያንስ 5 ከባደ የአካል ጉዳትና 3 ቀላል የአካል ጉዳት እንደሚያጋጥም ገልፀው የንብረት ውድመትን ጨምሮ በስድስ ወራት ውስጥ 16ሺ በላይ አደጋዎች አጋጥመዋል ብለዋል፡፡

በከተማችን አራት ዋና የሚባሉ የትራፊክ አደጋዎች የሚያጋልጡ የተለዩ መንስኤዎች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን ፍጥነት ገድብ በላይ ማሽከርከር፣ጠጥቶ ማሽከርከር፣ሞተር ሳይክሎች ሄልሜት ሳይጠቀሙ ማሽከርከር እና ስልክ እያወሩ ማሽከርከር አጋላጭ ሁኔታዎች ተብለው የተለዩ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ለበለጠ እና ሌሎች ትኩስ መረጃዎች ከስር ባሉት ሊንኮች በመግባት ቤተሰብ ይሁኑ።

ዌብሳይት ፡- https://www.afetanegari.com

በቴሌግራም ፡- https://t.me/afetanegari

ፌስቡክ ፡- https://www.facebook.com/afetanegari21

ዩቱዩብ:- https://youtube.com/@Afeta_Negari

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *