ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ::

ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 13ኛው መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሹመትን መርምሮ አፅድቋል።

በዚህም መሠረት በውሳኔ ቁጥር 14 እና 15/2015 ዓ.ም በ2 ድምጸ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ወ/ሮ ዛህራ ዑመር ዓሊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *