የወጣቶች ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው፡፡

ፌስቲቫሉ “ዛሬን በንቃት፣ ነገን በስኬት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን ሚያዚያ 21 እና 22, 2015 ዓ.ም በአዲሰ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚሰናዳው በዚህ ፌስቲቫል ወጣቶች በበርካታ በሙያ እና ጥረታቸው ለስኬት ከበቁ ሰዎች ወጣት የስራ ፈጠራ ባለሙያዎች እና በንግዱ ዘርፍ ውጤታማ ከሆኑ ኢትዮጵያዊያን ጋር የሚገኛኙበት እና ልምድ የሚለዋወጡበት እድል ተመቻችቷል፡፡

ወጣቶች በቴክኖሎጅ፣ በንግድ እና በስራ ፈጠራ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማዳበር የሚረዱ የስልጠና መድረኮችም ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

ከዚህ ባሻገር ፌስቲቫሉ የወጣቶችን ጤና እና ደህንነት፡ መልካም ሰብእና የሚገነቡ ልዮ ልዩ ሰፓርታዊ እንቅስቃሴዎችን፣ ጨዋታዎችን (ጊሞች)፣ የሥነ-ሰአል እና ፎቶ ጋላሪ የተክኖሎጅ መንደር ኮርነር)፣ ከተሊያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የመጡ ልዩ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች ያላቸውን የተለየ አቅም እና ችሎታ የሚያሳዩበት መድረኮችን ጨምሮ የንግድ ትርኢትን ያከተተ ነው።

በዚህ የወጣቶች ፌስቲቫል ስመ-ጥር ኢትዮጵያዊያን የሙዚቃ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ትልቅ የሙዚቃ ድግስ እና የኮሜዲያ ስራዎችም እንደሚቀርቡ ተነግሯል፡፡

ይህ ዝግጅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወጣቶችን በልዩ ልዩ መንገድ ለመደገፍ በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮግራም ትግበራ አካል ነው፡፡

ፌስቲቫሉ በአምሬፍ ሔልዝ አፍሪካ እና የከፍታ ኮንሶርትየም አባላት አስተባባሪነት ታቅዶ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከሜላ ኤቨንትስ፣ ከሴቶች አና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒሰቴር፣ ከአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከሌሎች ልማት አጋሮች እና ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር የሚዘጋጅ ነው።

የውልሰው ገዝሙ
መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *