መንግስት በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ

መንግሥት በሱዳን ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናው መስሪያ ቤት እና ካርቱም በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ አማካኝነት የኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ለመጠበቅ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና አጎራባች ክልሎች አባል የሆኑበት ግብረ ኃይል በሀገር አቀፍ ደረጃ መቋቋሙም ነው የተመለከተው፡፡

አስፈላጊ መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 12ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.