በአማሮ ወረዳ የሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ተበድያለው ሲል ቅሬታውን አሰማ፡፡

በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ውስጥ የሚገኘው የአማሮ ወረዳ የበዳንሶ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ባስመዘግብም እወቅና አልተቸረኝም ሲል ከሷል፡፡

ትምህርት ቤቱ ቅሬታውን ያሰማው ከሚጠበቀው በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ያፈሩ መሰል ትምህርት ቤቶች መሸለማቸው ተገቢ አይደለም ሲል ነው፡፡

አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ ያላስገባ ትምህርት ቤት የዕውቅናና ሽልማት አግኝቷል ሲሉም የትምህርት ቤቱ መምህራንና ርዕሰ መምህራኖች ለጣቢያችን ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ተደጋጋሚ የህግና ደንብ ጥሰቶች በትምህርት ቤቱ መምህራን ላይ እንደሚፈጸም የትምህርት ቤቱ መምህራን ገልፀዋል፡፡

የአማሮ ልዩ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ አያሌው አሳምነው በበኩላቸው ቅሬታው በሬ ወለድ ነው ሲሉ ለጣብያችን የገለፁ ሲሆን የክልሉ መንግስት በወላይታ ሶዶ በነበረ ጉባኤ ላይ ተወካዮች እንድንልክ የተጠየቀን ሲሆን እኛም አንድ ተማሪ እና አንድ መምህር በአጠቃላይ አምስት ተወካዮችን ከየትምህርት ቤቱ ወክለን ልከናል ብለዋል፡፡

አቶ አያሌው አክለው ዕውቅናና ሽልማቱ 550 እና ከዚያ በላይ ላመጡ ተማሪዎች እንጂ ለመምህራንም ሆነ ለሌላ አካል የተሰጠ ሽልማት የለም ብለዋል፡፡

የወረዳው የትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት በትምህርት አሰጣጥ ሂደታቸው ዝቅ ያለ አፈፃፀም ያላቸውን ትምህርት ቤቶች ተመርጠው ልምድ እንዲወስዱ ከማድረግ በዘለለ የተለየ ጥቅም እንዲያገኝ የተመረጠ አካል የለውም ሲሉ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡

የፅ/ቤቱ ም/ል ሀላፊ ችግሩን በመወያየት እንፈታው በማለት በተደጋጋሚ ለማወያየት ብንሞክርም ቅሬታ አቅራቢዎች ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ሲሉ ምላሻቸውን ሰተውናል፡፡

አቤል ደጀኔ
ሚያዝያ 12ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.