በኮንትሮ ባንድ ንግድ ላይ የጸጥታ አካላት እጃቸው የረዘመ በመሆኑ የኮትሮ ባንድ ንግድ መቀነስ አልተቻለም ሲል የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮንትሮ ባንድ ንግድ ላይ የጸጥታ አካላት እየተሳተፉ ነው ሲል የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በጉሙሩክ ኮሚሽን የኢንተለጀንስ እና ኮንትሮባንድ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ ኢትዮጵያ በየጊዜው በኮንትሮባንድ ንግድ የምታጣው ገቢ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

በፀጥታ አካላት የሚደግፉት የኮንትሮባንድ አሳላፊዎችና ነጋዴዎች ቁጥራቸው እየተበራከተ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ተገኔ ችግሩን ለመቆጣጠርና ለመከላከል አዳጋች ሆኗል ብለዋል፡፡

ኮንትሮባንድ የመከላከል ኃላፊነት የተሰጠው ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ ሳይሆን የጸጥታ አካላት ጭምር በመሆናቸው ሃላፊነታቸው በታማኝነት ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ስምንት ወራቶች ውስጥም ሁለት ኮኖኔሎች እና ሌሎችም የክልል የጸጥታ አካላት በኮንትሮባንድ ንግድ ተሳትፈው ተይዘዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተያዘው በበጀት አመቱ ስምንት ወራቶች ውስጥ 5 ቢሊዮን ብር ከኮንትሮ ባንድ ንግድ ማዳን እንደተቻለም አቶ ተገኔ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በሄኖክ ወልደ ገብርኤል

ሚያዝያ 12ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.