የፌዴራል ጠቅላይ ሽሪዓ ፍርድ ቤት የዘንድሮው የኢድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሐሙስ ማታ ሚያዚያ 12/2015 ከታየች ዓርብ ሚያዚያ 13/2015ዓ.ም ተከብሮ ይውላል ያለ ሲሆን ነገር ግን ጨረቃ ሐሙስ ካልታየች ኢድ አል ፈጥር ቅዳሜ ሚያዚያ 14/2015 ዓ.ም እንደሚሆን አስታውቋል፡፡
ምክር ቤቱ ይህንን ያለው የ2015 የኢድ አልፈጥር በዓል አከባበር በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ሽሪዓ ፍርድ ቤት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፈበት ወቅት ነው።
በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው ዓመተ ሒጅራ ለሚከበረው የኢድ አል ፈጥር በዓል ዋዜማለሀገራችን ኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ በዓሉ የሰላም የደስታና የፍቅር እንዲሆንላቸው የተመኘው የፌዴራል ጠቅላይ ሽሪዓ ፍርድ ቤት የዘንድሮው የኢድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሐሙስ ማታ ሚያዚያ 12/2015 ከታየች ዓርብ ሚያዚያ 13/2015ዓ.ል ተከብሮ ይውላል ነገር ግን
ጨረቃ ሐሙስ ካልታየች ኢድ አል ፈጥር ቅዳሜ ሚያዚያ 14/2015 ዓ.ም እንደሚሆን አስታውቋል፡፡
በዓሉን በምናከብርበት ወቅት ሙስሊሙ ሕብረተሰብ የተቸገሩ ወገኖቻችን በማሰብና በመርዳት በመተዛዘን በዓሉ እንዲከብር በአላህ ስም እንጠይቃለን ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 12ቀን 2015 ዓ.ም











