በአስራ ሰባት ሺህ ተቋማት ላይ በተደረገ የአደጋ ስጋት ቁጥጥር 25 ተቋማት ብቻ አለም አቀፍ የአደጋ ስጋት ምዘና መስፈርት እንዳሟሉ የአዲጽስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ወልደመስቀል ለኢትዮኤፍኤም ተናግረዋል።
ለአመታት በተደረገው የአደጋ ስጋት እና ቁጥጥር 180 ባለኮከብ ሆቴሎች 13ቱ መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆን በከተማዋ ከሚገኙ 667 ፋብሪካዎች አምስቱ ብቻ አለም አቀፍ የአደጋ ምዘና መስፈት እንዳሟሉም ገልፀዋል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ በተቋማት ላይ ፍተሻ ማድረግ እና የምክክር አገልግሎት የሚሰጥ የነበረ ሲሆን በተቋማት ላይ የንግድ ፈቃድ እስከ ማገድ እና ተቋሙ አገልግሎት አንዳይሰጥ የማድረግ ህጋዊ እርምጃ በቅርቡ መውሰድ እንደሚጀመር ነግረውናል።
በመዲናዋ በሶስት ወራት ውስጥ 300 አደጋዎች የደረሰ ሲሆን በቅርቡ በሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ሊወድም መቻሉም በመድረኩ ተገልፆል።
አደጋን ለመከላከል እኛም ሚና አለን በሚል መሪ ቃል ለኪነጥበብ ባለሞያ እና ለሚዲያ ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
እሊኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም











