አንድንድ የትራፊክ ፖሊሶች የትራፊክ ህጉን የሚጥሱ የህግ አካላትን መቅጣት” ስራዬን አጣለው” የሚል ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል ተባሏል፡፡

የትራፊክ ህጉን እንዲያከብሩ ግዴታ የተጣለባቸው አንዳንድ የህግ አካላት ፤ህጉን ሲጥሱ እንደሚስተዋሉ የመንገድ ደንነት ባለሞያ የሆኑት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

የትራፊክ ህጉን የሚጥሱ የህግ አካላትን መቅጣት ደግሞ የትራፊክ ፖሊሶችን “ስራዬን አጣላው” የሚል ስጋት ውስጥ እንደሚከታቸው ገልጸዋል፡፡

ይህም እርሳቸው በነበሩበት የትራፊክ ፖሊስነት የስራ ዘመናቸው የገጠማቸው ነገር እንደሆነ አንስተዋል፡፡
የመንገድ ደንነት ባለሞያው እንደሚሉት ከሆነ አንዳንድ በመንግስት የስራ ሃላፊነት ላይ የሚገኙ አካላት በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ያልተፈቀዱ መንገዶችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል፡፡

ህግን በማክበር ግንባር ቀደም መሆን አለባቸው ተብለው ስለሚጠበቁ ህግን በሚጥሱበት ወቅት በማህበረሰቡ ዘንድ በቀላሉ ተጋላጭ እንዲሆኑ እንደሚያረጋቸው ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በትራፊክ ፖሊስነት የሚሰሩ ባለሞያዎች ቆራጥ ሆነው የትራፊክ ህጉን ሊያስከብሩ እና በመንግስት ሆነ በደንነት አካላት ሽፋን የትራፊክ ህግን የሚጥሱ አሽከርካሪዎችን ሊቀጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ካልሆነ ግን የነዚህ አካላት ለትራፊክ አደጋ የሚኖራቸው አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ አንስተዋል፡፡

መሳይ ገ/መድህን
ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.