ሩሲያ የአዉሮፓ ህብረትን አስጠነቀቀች

ሞስኮ የአዉሮፓ ህብረት የጦር ጎራ ከመሆን ሊታቀብ ይገባል ስትል አስጠንቅቃለች፡፡

የሩሲያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የአዉሮፓ ህብረት እራሱን ወደ ጦር ጎራ እየለወጠ ነዉ ሲሉ በኒዮርክ በነበረ መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

ህብረቱ እራሱን የጦር መሳሪያ እያስታጠቀ ለሩሲያ ስጋት እየሆነ እንደመጣም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታዉቀዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአዉሮፓ ህብረትና በኔቶ መካከል የተወሰነ ልዩነት ብቻ እንዳለም ላቭሮቭ አንስተዋል፡፡
በመሆኑም ህብረቱ ወደ ጦር ጎራነት ከመለወጠ እንዲታቅብ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት አባል ሀገራትና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ መስፋፋታቸዉን እንዳልገቱም ሞስኮ ገልጻለች፡፡

ለዚህም ላቭሮቭ እንደማሳያ ያነሱት የፊንላንድንና የስዊዲንን የአባልነት ጥያቄ ነዉ ሲል የዘገበዉ አልጄዚራ ነዉ፡፡

አባቱ መረቀ
ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *