በኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ህይወታቸው የሚያጡ ዜጎች የሞት ምጣኔ 43 በመቶ መሆኑ ተነገረ

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በዜጎች ጤና እና ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር አማካኝነት ለሚዲያ ባለሞያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተከናውኗል ።

በስልጠናውም ጤናማ ያልሆነ አመጋገብን በተመለከተ የተለያዩ የዳሰሳ ጥናቶች ቀርበዋል፤ በሀገራችን ስድስት በመቶ የሚሆነው ሞት ጤናማ ካልሆነ አመጋገብ ጋራ በተያያዘ እንደሚከሰት በጤና ሚንስትር ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ሙሴ ገብረሚካኤል ተናግረዋል።

በ15 አመታት ውስጥ የጨው ይዘት ቅነሳ ላይ ካልተሰራ የ455 ሺህ ሰዎች ህይወት አደጋ ላይ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን፤ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታውን ለመቆጣጠርም ከ242 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገልፆል።

ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ለመቆጣጠር የሚያስችል አስገዳጅ ህግ ማውጣት፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምርቶች የፊት ለፊት ማሸጊያዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች እንኖሩ ማስገደድ ፣ የገበያ ቁጥጥር ማረግ፣ የማስታወቂያ ገደብ መጣል እና ከፍተኛ ታክስ መጣል፤ የአለም የጤና ድርጅት ሃገሮች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ለመቆጣጠር ይረዳል በሚል ያስቀመጣቸው የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች መሆናቸው ተገልፆል።

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.