80ሚሊዮን ብር በኤልክትሮኒክስ ስርአት ተዘዋውሯል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር የነዳጅ ግብይት በኤልክትሮኒክስ ስርአት ካስጀመረበት ሰአት አንስቶ እስካሁን ድረስ 80 ሚሊዮን ብር ግብይት መፈጸሙን አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገድ እንዲሆን ከወሰነበት እለት ጀምሮ ከ43ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች መስተናገዳቸውን ገልጻል፡፡

የሚኒስትሩ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ስርአት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሳልማን ሞሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከኢትዮ ቴኮም ጋር በመተባበር የነዳጅ ግብይት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡

ገና ጅምር ላይ በመሆኑ የተወሰኑ ችግሮች ሊያጋጥሙ ግድ ይላል ያሉት አቶ ሳልማን በሂደት ሁሉም ይስተካከላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተጠቃሚዎች ወደ ነዳጅ ጣበያዎች ሲመጡ እንደ ሞባይል ባንኪንግ የመሰሉ የኤልክትሮኒክስ ስርአት የሚያስጠቅሙ መተግበርያዎችን ዳወን ሎድ በማድረግ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል፡፡

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ፍቃደኝነት ይጎላል ያሉት አቶ ሳልማን ነዳጅ ማደያዎች በመንግስት በኩል የተላለፈውን ውሳኔ ሊያከብሩ ግድ ይላል ብለዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.